መጋቢት ፳፮
መጋቢት ፳፮፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፮ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት የመጀመሪያው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፷ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፶፱ ቀናት ይቀራሉ።
ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች
- ፲፰፻፺፯ ዓ/ም - ‘የካንግራ ሸለቆ’ በሚባለው የሕንድ ግዛት ውስጥ የተከሰተው እሳተ ገሞራ የ ፳ ሺ ሰዎችን ሕይወት ሲያጠፋ የአካባቢውን ከተማዎችና ሠፈሮች አውድሟል።
- ፲፱፻፵፩ ዓ/ም - አሥራ ሁለት ምዕራባውያን አገሮች፤ የአሜሪካ ኅብረት፣ ታላቋ ብሪታንያ፣ ፈረንሲስ፣ ቤልጂግ፣ ሆላንድ፣ ዴንማርክ፣ ኢጣልያ፣ ሉክሳምቡርግ፣ ኖርዌይ፣ አይስላንድ፣ ካናዳ እና ብርቱጋል በስምምነት የሰሜን አትለንቲስ የውል ድርጅት (North Atlantic Treaty Organization (NATO) ) መሠረቱ
- ፲፱፻፷ ዓ/ም - በአሜሪካ የሰብዓዊ መብት ተሟጋችና የጥቁር አሜሪካውያን መሪ የነበረው ታናሹ ማርቲን ሉተር ኪንግ ጄምስ ኧርል ሬይ በተባል ነፍሰ ገዳይ እጅ በሜምፊስ ከተማ ተገደለ። የኪንግ ሞት ዜና ሲሰማ በ መቶ የአሜሪካ ከተሞች ከፍ ያለ የሕዝብ ሽብር ተከተለ።
ልደት
ዋቢ ምንጮች
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.