መጋቢት ፲፩

መጋቢት ፲፩፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፻፺፩ ኛው ዕለት ሲሆን፤ የበጋ ወቅት ፸፮ ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፸፭ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፸፬ ቀናት ይቀራሉ።

ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች

  • ፲፭፻፳፪ ዓ/ም - ከአህመድ ግራኝ ጋር ሽምብራኩሬ በተባለ ቦታ ላይ በተደረገ ጦርነት ራስ ኅዱግ፣ ራስ ማኅፀንቶ፣ ገብረ መድኅን እና ብዙ የኢትዮጵያ ሠራዊት አለቁ።
  • ፲፱፻፳፰ ዓ/ም - የፋሺስት ኢጣሊያ አውሮፕላኖች በኮረም ላይ የመርዝ ጢስ ቦንብ ጣሉ፡፡
  • ፲፱፻፵፮ ዓ/ም - የወንጂ ስኳር ፋብሪካ ተመርቆ ተከፈተ፡
  • ፳፻፪ ዓ/ም - የአፍሪቃ ኅብረት የሠላምና ጸጥታ ምክር ቤት በማዳጋስካር ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል በለወጡ ግለሰቦችና ተቋማት ላይ የተጣለው ማዕቀብ ተግባራዊ እንዲሆን ወሰነ፡፡


ልደት


ዋቢ ምንጮች

  • (እንግሊዝኛ) FCO 371/1829 - ANNUAL REVIEW FOR ETHIOPIA FOR 1974
  • (እንግሊዝኛ)


የኢትዮጵያ ወራት
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.