መዝገበ ዕውቀት

መዝገበ ዕውቀት (ኢንሳይክሎፒዲያ) ማለት ወይም የዕውቀት ዘርፎች ሁሉ ወይም የአንድ ዕውቀት ዘርፍ የመረጃ ክምችት ነው። ከመዝገበ ቃላት የሚለይበት ጥቅሙ እያንዳንዱ መጣጥፍ ስለ አንድ ቃል ወይም ዘይቤ ብቻ ሳይሆን ጥልቀት ያለው መረጃ እሚሰጥ መሆኑ ነው። ስለዚህ የመዝገበ ዕውቀት መጣጥፍ ከመዝገበ ቃላት መጣጥፍ ይልቅ ረጅምና ዝርዝሩን የሚገልጽ ነው። ከሁሉ ጥንታዊው እስካሁንም የሚገኘው መዝገበ ዕውቀት የፕሊኒ መጽሐፍ ናቱራሊስ ሂስቶሪያ ወይም «የተፈጥሮ ታሪክ» (69 ዓ.ም. በሮማይስጥ ተጽፎ) ይባላል። በአሁኑ ዘመን በኢንተርኔት የሚነቡ ብዙ መዛግብተ ዕውቀት (ለምሳሌ ውክፔዲያ) ሊገኙ ይቻላል።

ዕውቀት የተሳተ መረጃ ሊሆን እንደሚችል ሁሉ፣ መዝገበ ዕውቀት «መዝገበ ዕውነት» ከቶ አይሆንም። ለመሆኑ ግን በዞራስተር ጽሑፍ መሠረት «መዝገበ ዕውነት» (ሃታ-ማራኒሽ) የእግዚአብሔር 16ኛው ስያሜ ነው።

This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.