መካከለኛው ምሥራቅ
መካከለኛው ምሥራቅ ማለት አብዛኛው ጊዜ ዛሬ ከአረቢያ እስከ ቱርክ፣ ከግብጽ እስከ ፋርስ ያሉት አገራት ናቸው።
የአሜሪካ መንግሥት መጀመርያው «መካከለኛው ምሥራቅ» የሚለውን ስያሜ በይፋ የጠቀሙ በ1949 ዓም ሲሆን፣ ትርጉሙ «ከሊብያ እስከ ፓኪስታን፣ ከሶርያና ኢራቅ እስከ ሱዳንና ኢትዮጵያ» ተባለ። በሚከተለው ዓመት ግን በ1950 ዓም የ«መካከለኛው ምሥራቅ» ትርጉም ግብጽ፣ ሶርያ፣ እስራኤል፣ ሊባኖስ፣ ዮርዳኖስ፣ ኢራቅ፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ኩወይት፣ ባሕሬንና ቃጣር ብቻ እንደ ጠቀለለ ወሰነ። አሁንም እነዚህ አገራት ሁሉ ከቱርክ፣ ፋርስ፣ ቆጵሮስ፣ የመን፣ ኦማንና የተባበሩት የዓረብ ግዛቶች ጭምር በዘልማድ «መካከለኛው ምሥራቅ» ይባላሉ።
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.