መተሬ

መተሬ (ሮማይስጥGlinus lotoides) ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ነው። የኮሶ መድኃኒት ነው።

?መተሬ

ሳይንሳዊ ደረጃ መስጫ
ስፍን: Plantae
(unranked) Eudicots
(unranked) Core eudicots
ክፍለመደብ: Caryophyllales
አስተኔ: Molluginaceae
ወገን: Glinus
ዝርያ: G. lotoides
ክሌስም ስያሜ
''Glinus lotoides''
L.

በብዛት የሚገኝበት መልክዓ ምድር

በኢትዮጵያ፣ በተለይ በቆላ ወንዝ ደለሎች ለምሳሌ በዋቤ ሸበሌ ወንዝ ባለው ከላፎ ደለል ይገኛል።

የተክሉ ጥቅም

የኮሶ ትል ለማስወጣት በሰፊ ይጠቀማል፣ በገበያም ይሸጣል።[1]

ደብረ ሊባኖስ ዙሪያ በተደረገ ጥናት መሠረት፣ ትሉን ለማስወጣት፣ ቅጠሉ ወይስ ዘሩ ተደቅቆ በውሃ ይጠጣል። ይህም ከብሳና ልጥ ጋር ሊጠጣ ይችላል። ዘሮቹም ደግሞ ከኑግ ዘር ጋር በለጥፍ ይበላል።[2][3]


  1. አማረ ጌታሁን - SOME COMMON MEDICINAL AND POISONOUS PLANTS USED IN ETHIOPIAN FOLK MEDICINE Archived ጁላይ 31, 2017 at the Wayback Machine March 1976 እ.ኤ.አ.
  2. በደብረ ሊባኖስ ዙሪያ ያለው ሕዝብ መድሃኒታዊ እጾች እውቀናና ጥቅም 1998 ዓም ከጥላሁን ተክለሃይማኖት፣ ሚሩጸ ጊዳይ፣ ግርማይ መድኅን፣ ያለም መኮነን፣ አዲስ አበባ ዩኒቬርሲቴ፣ አክሊሉ ለማ ተቋም
  3. የዘጌ ልሳነ ምድር ባህላዊ መድሃኒት ጥናት 1999 ዓም ከጥላሁን ተክለሃይማኖት፣ ሚሩጸ ጊዳይ፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.