መስኪያጝካሸር
መስኪያጝ-ካሸር (ወይም መሽ-ኪአጝ-ጋሸር) በሱመራዊ ነገሥታት ዝርዝር ዘንድ የኤንመርካር አባትና የኤአና ንጉሥ ነበር። እንዲህ ሲል፦
- «በኤአና መስኪያጝ-ካሸር የኡቱ ልጅ ገዢና ንጉሥ ሆነ፤ ለ324 (ወይም 325) አመታት ነገሠ። መስኪያጝ-ካሸር ወደ ባሕር ገብቶ አልታየም። የመስኪያጝ-ካሸር ልጅ ኤንመርካር ኡሩክን ሠርቶ የኡሩክ ንጉሥ ሆነ።»[1]
«ኡቱ» ማለት የፀሐይ አምላክ ወይም ጣኦት ሲሆን «ኤ-አና» ማለት የኡሩክ ከተማ አምባ ወይም ቤተ መቅደስ ነበር። እንደ ተከታዮቹ ኤንመርካር፣ ሉጋልባንዳ፣ ዱሙዚድ፣ አሣ አጥማጁ ወይም ጊልጋመሽ ሳይሆን፣ የመስኪያጝ-ካሸር ስም ከሌላ አፈ ታሪክ ወይም ሰነድ ከነገሥታት ዝርዝር በቀር አይታወቅም። ኤንመርካርና የአራታ ንጉሥ በሚባለው አፈታሪክ ዘንድ ግን፣ ኤንመርካር እራሱ የኡቱ ልጅ ይባላል፤ ኤንመርካር ደግሞ የኡሩክና የኤሪዱ መስራችና ጽሕፈትን የፈጠረው ንጉሥ ይባላል።
በመምህሩ ዴቪድ ሮህል አስተሳሰብ ዘንድ፣ የመስኪያጝ-ካሸር መታወቂያ ከኩሽ (የካም ልጅ) ጋር አንድላይ ያደርገዋል።[2]
ቀዳሚው የለም |
የኤአና ንጉሥ (ሉጋል) ከ2470 ዓክልበ. በፊት ወይም አፈታሪካዊ |
ተከታይ ኤንመርካር |
ተዋቢ ምንጮች
- Electronic Text Corpus of Sumerian Literature
- Legend: Genesis of Civilisation Arrow Books Ltd, London, 1999, pp. 451-452.
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.