መስኪአጝ-ናና

መስኪአጝ-ናና ከ2182 እስከ 2152 ዓክልበ. ድረስ ግድም የኡር ንጉሥና የሱመር አለቃ ነበረ።

በአንዳንድ የሱመራዊ ነገሥታት ዝርዝር ቅጅዎች ለ48 ዓመታት ነገሠ፤ እነዚህ ቁጥሮች ግን ምንም ታማኝነት የላቸውም። ከርሱ ዘመን ቀጥሎ «ያንጊዜ ኡር ተሸነፈና ላዕላይነቱ ወደ አዳብ ተወሰደ» ይላል፤ የአዳብ ንጉሥ ሉጋል-አኔ-ሙንዱ መንግሥት ይከተላል።

የመስኪአጝ-ናና ስም አለዚያ የሚታወቀው የቱማል ጽሑፍ በተባለው ሰነድ ውስጥ ይጠቀሳል። በዚህ በኩል መስኪአጝ-ናና የኒፑር መቅደስ እንደ ጠገነ ሲለን፣ እንግዲህ የሱመርን ላዕላይነት በውነት እንደ ያዘ ይመስላል።

ቀዳሚው
ኡር ንጉሥ ናኒ
ሱመር (ኒፑር) አለቃ
2182-2152 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
አዳብ ንጉሥ ሉጋል-አኔ-ሙንዱ
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.