መሮ
መሮ ከፌሮ ብረት ቁራጭ የሚሰራ እና በተለይም እንጨትን ለመፈልፈል እና ለመብሳት የሚያገለግል ሹል ብረት ነው። ይህ ብረት ለማገር፣ ጠርብ፣ አውራጅ ወይንም ሌላ የመዋቅር አይነቶች መብሻነት አልያም ደግሞ እንደ ግንብ ላሉ መዋቅሮች መፈልፈያነት ይጠቅማል። ይህ መሳሪያ በመዶሻ ወይንም መርቴሎ እየተመታ መዋቅሮቹን እንዲፈለፍል ወይም ወደ ውስጥ እንዲገባ ይደረጋል።
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.