መርነፈሬ አይ
መርነፈሬ አይ ግብጽ በ2ኛው ጨለማ ዘመን (13ኛው ሥርወ መንግሥት) ምናልባት ከ1665 እስከ 1661 ዓክልበ. ግድም ድረስ የገዛ ፈርዖን ነበረ።
መርነፈሬ አይ | |
---|---|
የመርነፈሬ ቅርስ | |
የግብጽ ፈርዖን | |
ግዛት | 1665-1661 ዓክልበ. ግ. |
ቀዳሚ | ዋሂብሬ ኢቢያው |
ተከታይ | መርሆተፕሬ ኢኒ |
ሥርወ-መንግሥት | 13ኛው ሥርወ መንግሥት |
የቶሪኖ ቀኖና በተባለው ዝርዝር ዘንድ፣ ዘመኑ ለ፳፫ ዓመታትና ፰ ወር ቆየ፤ ዳሩ ግን ለዘመኑ ቅርሶቹ ወይም ፍርስራሶቹ ጥቂት በመሆናቸው እስከዚያ ያህል ድረስ መግዛቱ አጠራጣሪ ነው። የግብጽ ታሪክ መምህሮች እንደሚያውቁ በዘመኑ መጨረሻ «አስተዳደሩ ፈጽሞ ወድቆ ነበር ይመስላል»። ዋና ከተማው እጅታዊ ከርሱ በኋላ ተተወ፣ ተከታዮቹም የጤቤስ ገዦች ብቻ እንጂ የመላውን ግብጽ ፈርዖኖች አልነበሩም። የዚህ ምክንያት የግብጽ ሃይል እጅግ ተደክሞ ሂክሶስ የተባለው አሞራዊ ወገን በዚያን ጊዜ በስሜን ወረራ ስላደረገ ነው።
የመርነፈሬ አይ መቃብር እስካሁን መቸም አልተገኘም።
ቀዳሚው ዋሂብሬ ኢቢያው |
የግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን 1665-1661 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ መርሆተፕሬ ኢኒ |
ዋቢ ምንጭ
- K.S.B. Ryholt: The Political Situation in Egypt during the Second Intermediate Period, c. 1800 – 1550 BC, Carsten Niebuhr Institute Publications, vol. 20. Copenhagen: Museum Tusculanum Press, 1997 (እንግሊዝኛ)
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.