መርሆተፕሬ ኢኒ

መርሆተፕሬ ኢኒ ግብጽ2ኛው ጨለማ ዘመን (13ኛው ሥርወ መንግሥት) ምናልባት ከ1661 እስከ 1659 ዓክልበ. ግድም ድረስ የገዛ ፈርዖን ነበረ።

መርሆተፕሬ ኢኒ
የመርሆተፕሬ ስም በጥንዚዛ ቅርጽ
የመርሆተፕሬ ስም በጥንዚዛ ቅርጽ
የግብጽ ፈርዖን
ግዛት 1661-1659 ዓክልበ. ግ.
ቀዳሚ መርነፈሬ አይ
ተከታይ ሰዋጅተው
ሥርወ-መንግሥት 13ኛው ሥርወ መንግሥት

ስለ ፈርዖን ኢኒ ብዙ አይታወቅም። የቶሪኖ ቀኖና በተባለው ዝርዝር ዘንድ፣ ዘመኑ ለ፪ ዓመታትና ፫ ወር፣ ፱ ቀን ብቻ ቆየ። ዘመኑ አጭር ቢሆንም ስሙ በአንድ ጥንዚዛና በአንድ ጋን ክዳን ላይ ተገኝቷል። ደግሞ በአንድ ጽላት ላይ («የካይሮ ፍትሓዊ ጽላት») ከፈርዖን ነቢሪራው 1ኛ ዓመት (1635 ዓክልበ.) ሲሆን አያመሩ የተባለ መኮንን የኤል-ካብ አገረ ገዥ በመርሆተፕሬ 1ኛ አመት (1661 ዓክልበ.) እንደ ተሾመ ይጠቅሳል።

በዚሁም ዘመን ዋና ከተማው እጅታዊ ተተወ፣ ኢኒ የጤቤስ አካባቢ ገዥ ብቻ እንጂ የመላውን ግብጽ ፈርዖን እንደ ነበር አይመስልም። የዚህ ምክንያት የግብጽ ሃይል እጅግ ተደክሞ ሂክሶስ የተባለው አሞራዊ ወገን በዚያን ጊዜ በስሜን ወረራ ስላደረገ ነው።

ቀዳሚው
መርነፈሬ አይ
ግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን
1661-1659 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ሰዋጅተው

ዋቢ ምንጭ

  • K.S.B. Ryholt: The Political Situation in Egypt during the Second Intermediate Period, c. 1800 – 1550 BC, Carsten Niebuhr Institute Publications, vol. 20. Copenhagen: Museum Tusculanum Press, 1997 (እንግሊዝኛ)
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.