ሐምሌ ፳፬
በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፳፬ ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ዮሐንስ ፵፪ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ማቴዎስ፤ ማርቆስ እና ሉቃስ ደግሞ ፵፩ ዕለታት ይቀራሉ።
ታሪካዊ ማስታወሻዎች
፲፮፻፲፩ ዓ/ም የመጀመሪያዎቹ አፍሪቃውያን ”ተገዳጅ ሎሌዎች” ወይም ባሪያዎች በዩናይትድ ስቴትስ ጄምስ ታውን፣ ቨርጂኒያ የሚባል ሥፍራ ላይ ከመርከብ ወረዱ።
፲፯፻፷፮ ዓ/ም ጦቢዛ[1] (Oxygen) የተባለው “ቶስመክ”[2] (element) ጆሴፍ ፕሪስትሊ በሚባል እንግሊዛዊ ተገኘ።
፲፯፻፺፫ ዓ/ም የታላቋ ብሪታንያን እና የአየርላንድን ንጉዛቶች [3] በማዋሃድ የአሁኗን የታላቋ ብሪታንያና የሰሜን አየርላንድ ንጉዛት ያስፈጠረው ሕግ ጸደቀ።
፲፰፻፳፮ ዓ/ም በጠቅላላው የብሪታንያ ንጉዛቶች “ተገሎሌ"[4] ወይም ባርነትን የሚደመስሰው ሕግ ተደንግጎ ጸደቀ። ሆኖም ሠራተኛ ያልሆኑ ተገሎሌዎች ሕጉ በጸደቀ በአራት ዓመቱ በዚሁ ዕለት በ፲፰፻፴ ዓ/ም ነጻነታቸውን ሲያገኙ ሠራተኛ ተገሎሌዎች ደግሞ ስድስት ዓመት ቆይተው በዚሁ ዕለት በ፲፰፻፴፪ ዓ/ም ነጻ ወጡ።
፲፱፻፶፪ ዓ/ም ዳሆሚ ትባል የነበረችው የአሁኗ ቤኒን ነጻነቷን ከፈረንሳይ ተቀዳጀች።
፲፱፻፶፭ ዓ/ም በኮንጎ ሽብር የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታ አስከባሪ ጦር ኃይሎች ጠላይ አዛዥ ሆነው ያገለገሉት ሌተና ጄኔራል ከበደ ገብሬ የሥልጣን ጊዜያቸውን በዚህ ዕለት አጠናቀቁ።[5]
፲፱፻፶፮ ዓ/ም የቀድሞዋ የቤልጅግ ኮንጎ ስሟ ተለውጦ የኮንጎ ሪፑብሊክ ተባለች።
ልደት
ዕለተ ሞት
ዋቢ ምንጮች
- መስፍን አረጋ (ዲባቶ )"ሰገላዊ አማርኛ" ፣ (፳፻ ዓ/ም) ገጽ 90፣
- መስፍን አረጋ (ዲባቶ )"ሰገላዊ አማርኛ" ፣ (፳፻ ዓ/ም) ገጽ 41
- ንጉሣዊ እና ግዛት የሚሉትን ቃላት በማጣመር kingdom ለሚለው ቃል ፍቺ እንዲሆን የተፈጠረ
- ተገዳጅ እና ሎሌ የሚሉትን ቃላት በማጣመር slave ለሚለው ቃል ፍቺ እንዲሆን የተፈጠረ
- (እንግሊዝኛ)P.R.O., FCO 371/178551 Annual Review of 1963