ሐምሌ ፳፩
ሐምሌ ፳፩ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፳፩ኛው ቀን ሲሆን የክረምት ወቅት ፳፮ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፵፭ ቀናት፣ በዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፵፬ቀናት ይቀራሉ።
ታሪካዊ ማስታወሻዎች
- ፲፱፻፰ ዓ/ም - ልጅ ኢያሱ ዓርብ በሌሊት ከአዲስ አበባ ተነሥተው በምድር ባቡር ድሬ ዳዋ ገቡ። የእንግሊዝ ዋና መላክተኛ ሚኒስትር ዊልፍሬድ ተሲገር ወደሎንዶን በላከው ምስጢራዊ ደብዳቤ ላይ ከልጅ ኢያሱ ጋር ራስ ልዑል ሰገድ እና ደጃዝማች ባልቻ ከሌሎች ተከታዮች ጋር አቃቂ ባቡር ጣቢያ ቅዳሜ ጧት ተሳፈሩ ብሏል። ልጅ ኢያሱ፤ በወቅቱ አላወቁትም እንጂ፣ ርዕሰ ከተማዋን ለመጨረሻ ጊዜ ያዩዋትም በዚህ ዕለት ሲሆን እዚያው ሐረርጌ ውስጥ እያሉ በመጪው መስከረም የመስቀል ዕለት ከሥልጣናቸው ተሻሩ።
- ፲፱፻፷፫ ዓ/ም - ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ለቀድሞው የላይቤሪያ ፕሬዚደንት ዶ/ር ዊሊያም ተብማን የቀብር ሥነ ሥርዓት ሞንሮቪያ ከተማ ገቡ።
- ፲፱፻፷፰ ዓ/ም - በቻይና፤ ከቤዪጂንግ ሰሜናዊ ምሥራቅ በምትገኘው ታንግሻን የተባለች ከተማ አካባቢ የተከሰተው የመሬት እንቅጥቅጥ እስከ ፯፻፶ ሺ ሰዎች ሕይወታቸውን እንዳጡ ተገምቷል።
ልደት
ዕለተ ሞት
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.