ሐምሌ ፲፮

ሐምሌ ፲፮ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፲፮ ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፶ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፶፩ ቀናት ይቀራሉ።

አቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች

፲፱፻፳፩ ዓ/ም የኢጣልያፋሽስት መንግሥት የሌላ ቋንቋ ወይም ባዕድ ቃላትን መጠቀምን ህገ ወጥ አድርጎ ደነገገ። (ኢትዮጵያም እንዲህ አይነት ህግ ባወጣች!!!!)

፲፱፻፵፬ ዓ.ም በጋማል አብደል ናስር የተመሠረተው የግብጽ የመኮንኖች እንቅስቃሴ በ ጄነራል ሙሐመድ ናጊብ መሪነት ንጉሥ ፋሩቅን ገለበጠ።

፲፱፻፷፮ ዓ/ም የግሪክ ወታደራዊ መንግሥት ውድቅ ሆኖ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስቴር ኮንስታንቲን ካራማንሊስ መንግሥት እንዲመሠርቱ ተጋበዙ።

፲፱፻፺፩ ዓ/ም የሞሮኮው አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን አል ሓሳን አባታቸው ሲሞቱ ንጉሥ ሞሐመድ አራተኛ ተብለው የንጉሥነት ዘውድ ጭነው ነገሡ።

ልደት

፲፰፻፹፬ ዓ/ም የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ፡ኃይለ፡ሥላሴሐረርጌ ውስጥ ኤጀርሳ ጎሮ ላይ ተወለዱ።

ዕለተ ሞት

፲፱፻፺፩ ዓ/ም የሞሮኮው ንጉሥ ዳግማዊ ሀሰን በተወለዱ በ ሰባ ዓመታቸው አረፉ። ዳግማዊ ሀሰን በ ፲፱፻፶፮ ዓ/ም አዲስ አበባ ላይ የተመሠረተውን የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት ከመሠሩት ሠላሳ አምስት መሪዎች አንዱ ነበሩ።

ዋቢ ምንጮች


የኢትዮጵያ ወራት
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.