ሐምሌ ፪
ሐምሌ ፪ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፪ ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፷፬ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፷፫ ቀናት ይቀራሉ።
አቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች
፲፭፻፴፫ ዓ/ም - ኢትዮጵያን የወረረውን ግራኝ መሐመድን ለመከላከል የዘመተውን የ|ብርቱጋል ሠራዊት የመራው ኤስቴቫዎ ዳጋማ ወንድሙን ክሪስቶቫዎ ዳጋማ ን ከአራት መቶ ወታደሮችና መቶ ሃምሳ ባሪያዎች ጋር ትቶ ከምጽዋ ወደብ ወደአገሩ ተጓዘ።
፲፱፻፴፱ ዓ/ም - የእንግሊዝ ልዕልት፣ (አሁን ዳግማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥ) እና የሌፍተናንት (አሁን የኤዲንበራ መስፍን ልዑል) ፊሊፕ የጋብቻ እጭት ይፋ ተደረገ።
፲፱፻፹፫ ዓ/ም - የደቡብ አፍሪቃ ሪፑብሊክ ለሠላሳ ዓመታት ከተገለለችበት የኦሊምፒክ ማሕበር ተመልሳ አባል ሆነች።
፲፱፻፺፬ ዓ/ም - የቀድሞውን የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት የተካው የአፍሪቃ ኅብረት አዲስ አበባ ላይ ተመሠረተ። የደቡብ አፍሪቃው ፕሬዚደንት ጻቦ እምቤኪ የኅብረቱ የመጀመሪያው ሊቀ መንበር ሆነው ተመረጡ።
ልደት
፲፱፻፯ ዓ.ም - ስመ ጥሩው ኢትዮጵያዊ አርበኛ እና የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ሊቀ መንበር የነበሩት ክቡር ደጃዝማች ኪዳኔ ወልደመድኅን ቡልጋ፣ ልዩ ስሙ ቡሄ ዓምባ በተባለ ሥፍራ ተወለዱ።
፲፱፻፰ ዓ/ም - ከ፲፱፻፷፫ ዓ/ም እስከ ፲፱፻፷፯ ዓ/ም የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ሰር ኤድዋርድ ሂዝ
፲፱፻፳፩ ዓ/ም - የቀድሞው የሞሮኮ ንጉሥዳግማዊ ሀሳን(አረብኛ: الحسن الثاني)። ንጉሡ የዛሬው የንጉሥ ሞሀመድ ራብእ (አረብኛ: محمد السادس) አባት ናቸው።
፲፱፻፴፬ ዓ/ም - ሪቻርድ ራውንድትሪ (Richard Roundtree). ሪቻርድ በዋና ተዋናይነት <<ጆን ሻፍት>> (John Shaft) ሆኖ <<ሻፍት ኢን አፍሪካ>> (Shaft in Africa) በተባለው ፊልም ላይ ከዘነበች ታደሰ (ሸርሙጣ ሆና) እና ደበበ እሸቱ (ዋሳ Wassa) ጋር ሠርቷል፡
ዕለተ ሞት
ዋቢ ምንጮች
- (እንግሊዝኛ) http://en.wikipedia.org/wiki/July 9
- (እንግሊዝኛ) http://www.imdb.com/title/tt0070679/
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |