ልብ
ልብ ማናቸውም የጀርባ አጥንት ባላቸው እንስሳት የሚገኝ ብልት ነው። የሰው ልጅ ልብ እጅግ ጠንካራ ከሆነ ጡንቻ የተሰራ ሲሆን መጠኑም ጭብጥ እጅን ያክላል። ልብ ደምን በደም ቦምቧ በመርጨት የሚያሰራጭ ፐምፕ ነው። ይህንም ሲያደርግ፣ በቋሚ ድግግሞሽ በመጨማተር እና በመላላት ነው።
መዋቅር
የሰው ልጅ ልብ 4 እልፍኞች/ክፍሎች አሉት። የአንድ አንድ እንስሳት ልብ 2 ወይንም 3 ብቻ እልፍኞች ይኖሯቸዋል።
በሰው ልጅ ልብ ውስጥ አራቱ እልፍኞች፣ በሁለት ይመደባሉ፣ እነርሱም ሁለቱ አትርየሞች እና ሁለቱ ቬንትሪክሎች ናቸው። የቀኝ አትሪየም እና የግራ ቬንትሪክል፣ ከሰውነት ወደ ልብ የሚመጣውን ደም ይቀበሉና፣ ወደ ሳምባ ደሙን ይልካሉ፤ እንዲጣራ ወይንም በሌላ አነጋገር አየር እንዲያገኝ። የተላከው ደም ሳምባ ውስጥ የተቃጠለ አየሩን ካራገፈ በኋላ በምትኩ ኦክሲጅን ይጭንና ተመልሶ ወደ ልብ ይመጣል። ይህ ከሳንባ የመጣ ደም ወደ ግራ አትሪየም እና ቬንትሪክል እልፍኞች ይጓዛል። እኒህ ሁለት እልፍኞች ልብ ሲኮማተር (ሲመታ) የተጣራውን ደም ወደ መላው የሰውነት ክፍል ያስራጫሉ።
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.