ሉጋልባንዳ

ሉጋልባንዳ «እረኛው» በሱመር ነገሥታት ዝርዝር ዘንድ የኡሩክ ሁለተኛ ንጉሥ ነበረ። 1200 አመታት እንደ ነገሠ ይጨምራል።

ስለ ሉጋልባንዳ የሚናገሩ ሁለት የሱመርኛ ትውፊቶች በሸክላ ጽላት ተገኝተዋል፤ እነርሱም በሊቃውንት «ሊጋልባንዳ በተራራ ዋሻ» እና «ሉጋልባንዳና የአንዙድ ወፍ» ይባላሉ።

በ«ሊጋልባንዳ በተራራ ዋሻ»፣ የኡሩክ ንጉሥ ሆኖ የቀደመው ኤንመርካር ሠራዊቱን በአራታ ላይ እንዲዘመት ያሠልፋል፤ ሉጋልባንዳ ከጦር አለቆቹ አንዱ ነው። ነገር ግን የኡሩክ ሠራዊት ወደ አራታ ሲሄድ በረጅም ተራሮች አልፎ፣ ድንገት ሉጋልባንዳ ተዝለፈለፈ። ሊያንቁት አይችሉምና ጓደኞቹ በዋሻ ውስጥ ከስንቅና ከዕጣን ሙጫ ጋር ይተዉትና መንገዳቸውን ይቀጥላሉ። ሉጋልባንዳ በዋሻው ትንግርት ሕልም ያያልና ይጸልያል፣ የጽሑፉ መጨረሻ ግን አሁን ፍርስራሽ ሆኖ በደንብ ሊነብ አይችልም።

በ«ሉጋልባንዳና የአንዙድ ወፍ»፣ ሉጋልባንዳ በሉሉቢ ተራሮች ሆኖ ደብዛው እስካሁን ጠፍቷል፤ ዳሩ ግን ታላላቁ የ«አንዙድ» ወፍ የኤንመርካርን ሠራዊት ዳግመኛ እንዲያገኝ ይረደዋል። የኤንመርካር ሠራዊት አራታን ለ1 አመት ቢከባትም፣ አይከናወንም። ኤንመርካር በኡሩክ መቅደስ ወዳለች ወደ ኢናና መልዕክት እንዲልክ ተልእኮ ይፈልጋል። ቀድሞ በኤንመርካር መንግሥት 50ኛው አመት የማርቱ ሕዝብሱመርና በአካድ በሙሉ በተነሡበት ጊዜ ግድግዳ በበረሃ እንዲሠራባቸው ስለ ረዳችው፣ እንደገና እርዳታዋን አሁን በአራታ ዘመቻው ይጠይቃታል። በመጨረሻ ሉጋልባንዳ ወደ ኡሩክ ኢንዲመልስ ፈቃደኛነቱን ይነግረዋልና መልዕክቱን ለኢናና ያደርሳል። የስዋ መልስ አራታና ምጣኔ ሀብቱ እንዴት እንደሚያዙ የሚል ምሳሌ ነው።

የጊልጋመሽ ትውፊት በተባለው አፈ ታሪክ ደግሞ፣ የኋለኛው ኡሩክ ንጉሥ ጊልጋመሽ እራሱን «የቅዱስ ሉጋልባንዳና የኒንሱን ልጅ» ይላል። በዚያ ዘመን፣ ሉጋልባንዳና ሚስቱ ኒንሱን እንደ አማልክት ተቆጠሩ።

ቀዳሚው
ኤንመርካር
ኡሩክ ንጉሥ (ሉጋል)
2406-2400 ዓክልበ. ግድም
(1,200 በአፈ ታሪክ)
ተከታይ
ዱሙዚድ፣ አሣ አጥማጁ

የውጭ ምንጮች

This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.