Þ

Þ, þ (þorn /ርን/) በአይስላንድኛ፣ በጥንታዊ እንግሊዝኛ እና በጥንታዊ ኖርስኛ የተገኘ ፊደል ነው።

በዘመናዊ እንግሊዝኛ እንዲሁም በዘመናዊ ስካንድናቪያ ልሳናት (ኖርዌኛስዊድኛዳንኛ)፤ የዚሁ ፊደል ድምጽ በሁለት ፊደላት በ«TH» በመወከሉ፣ የፊደሉ «Þ» ጥቅም ተተክቷል። «Þ» ዛሬ የሚታየው በአይስላንድኛ ጽሕፈት ብቻ ነው።

አጠራሩ በአማርኛ የማይሰማ ድምጽ ነው። ይህ ድምጽ ምላሱን ከላይኛው ጥርሶች በታች በመዘርጋት የሚፈጠር ነው። የውጭ ቋንቋ አጠራር በአቡጊዳ ጽሕፈት ለመግለጽ፣ ብዙ ጊዜ ይህ ድምጽ በ«» ወይም በ«» (ከነመስመሩ) ይወከላል።

ጥንታዊ እንግሊዝኛ አስቀድሞ ርክ በተባለው ሩን ጽሕፈት ይጻፍ ነበር። ክርስትናእንግሊዝ አገር ከተቀበለ በኋላ ግን፣ ቋንቋው በላቲን አልፋቤት ሊጻፍ ጀመረ። ይህ ድምጽ በሮማይስጥ ሰለማይታወቅ፣ በላቲን አልፋቤትም ለዚሁ ድምጽ ምንም ፊደል ባለመኖሩ፣ የ«Þ» ቅርጽ የተወሰደው ከፉርክ ጽሕፈት ከፊደሉ ነበር። ስሙም «ርን» (እሾህ) ከዚህ ሩን ስም ተወሰደ። በጥንታዊ ኖርስና አይስላንድኛ ደግሞ እንደዚያ ነበር፣ ነገር ግን የሩን ፊደል ስም «ርስ» (ረጃጅም) ይባል ነበር።

በነዚህ ልሳናት፣ አንድ ሌላ ፊደል «Ð, ð» ከ«Þ» ጋር የሚለዋወጥ ነበር። ሁለት የተለያዩ ድምጾች («» እና «») ቢወክሉም፣ ፊደሎቹ ግን አልተለያዩም። በዘመናዊ አይስላንድኛ ግን Þ ለ ፤ Ð ለ ይወሰናል።

የላቲን አልፋቤት
ABCDEF
GHIJKLM
NOPQRST
UVWXYZ
ተጨማሪ ምልክቶች፦
Þ...

በእንግሊዝኛ ከ1300 ዓ.ም. አካባቢ ጀምሮ፣ ድምጹ በሁለት ፊደላት (TH) መጻፍ ቄንጡ ሆነ። የ«Þ» ጥቅም እንግዲህ በየጥቂቱ ጠፋ። ሆኖም የእንግሊዝኛ ቃል «the» (መስተጻምሩ) ለረጅም ጊዜ «Þe» በመጻፉ ቆየ። በጊዜ ላይ፣ የዚህ አጻጻፉ እንደ «ye» ይመስል ጀመር። እስከ ዛሬም ድረስ፣ አንዳንድ ባለ ሱቅ ወይም ቡና ቤት የድሮ ባህል ሁኔታ ለማምሰል፣ በስማቸው ላይ «Ye Olde» («ጥንታዊው») ሲጨምሩ ከዚህ ልማድ የተነሣ ነው (ምሳሌ፦ «Ye Olde Pizza Parlor»፣ ወይም «ጥንታዊው ፒጻ ቤት»)። አብዛኞቹ ደንበኞች ግን የፊደሉን ታሪክ ባለማውቃቸው፣ አጠራሩ /ዪ ኦልድ/ እንደ ሆነ በማለት ይስታሉ።

ዋቢ መጻሕፍት

  • Freeborn, Dennis (1992) From Old English to Standard English. London: Macmillan

የውጭ መያያዣዎች

This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.